Skip to content
Home » ምስጋና

ምስጋና

ከሁሉ በፊት መልካም ሆኖ መልካምነትን በውስጣችን ላስቀመጠ ደግና ሩህሩህ አባት ለሆነው፤ኃያሉ እግዚአብሔር አምላካችንን በታላቅ አክብሮት እናመሰግነዋለን፡፡

ሁሉ በእርሱ ሆኗልና!!!

ውድ ሚስተር ጆሴፍ

ውድ ሚስተር ጆሴፍ፡ አንተ የፍቅር ለሕፃናትና ለእናቶች ድርጅት ትልቅ ስጦታ ነህ! ለተከታታይ አምስት ዓመታት በታላቅ ለጋስነትና በበጎነት ከጎናችን ሳትለይ አብረኸን ቆመሃል::ርቀት ሳይገድብህ፣ ዘር፣ ቀለም፣ ሳትል አንዳችም ምላሽ ሳትጠብቅ ሰው መቸገሩን ብቻ አይተህ ከሩቅ መጥተህ የብዙሃንን ህይወት ለውጠሃልና በመልካምነትህ ተጽዕኖ በለወጥካቸው እናቶች እና ሕፃናት ስም የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!!

ውለታህ ሁሌም በልባችን ይኖራል! አምላክ ብድራትህን ይክፈልህ!

ረጅም ዕድሜና ጤናን ይስጥህ!!!
እንወድሃለን!!!

ይህ መልዕክት የተዘጋጀው የረዳችሁንን ሁሉ ለማመስገን ነው::
ፍቅር ሆነን እንድናድግ ለዚህም እንድንበቃ ላደረጋችሁን ውድ ወላጆቻችን በጎነታችሁን ስናስብ ሁሌም እንደነቃለን፡፡ ለምታውቁትም ለማታውቁትም “የእግዜር እንግዳ” ብላችሁ ከማዕዳችሁ አካፍላችሁ እግር አጥባችሁ መኝታችሁን ሰጥታችሁ ሙሉ አቀባበል እያደረጋችሁ ለኖራችሁ ፍቅርን በተግባር አሳይታችሁናል፡፡ እንዲህ ላሳደጋችሁን ላልተነገረለት በጎ አድራጎታችሁ እና መልካምነታችሁ ከልባችን! እናመሰግናለን! ረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥልን ! ለምልሙልን!!!

* * * * * *

በመቀጠል በሀገርውስጥ ሆነ ከእሩቅ ሆናችሁ ምስኪን እናቶችንና ህፃናትን በፍቅር እጃችሁ የዳሰሳችሁ እንባቸውን ያበሳችሁ፣ከሙላታችሁ ሳይሆን ከጉድለታችሁ በማካፈል ወደእያንዳንዷ ተስፋ አጥ ቤት የገባችሁና በምግብ ባዶውን ማድጋ የሞላችሁና ጎዳና ላይ እንዳይወድቁ የቤት ኪራይ የከፈላችሁ ለድሆች ተስፋ ለሆናችሁ ውድ ኢትዮጵያውያንና ወገኖቻችን ቤተሰብ፣ ጓደኝ፣ ዘመድ እና ሌሎችም በጎ ያደረጋችሁ ሁሉ:- የአክብሮት መልዕክታችን ይድረሳችሁ እንላለን:: ላደረጋችሁት ሁሉ ሁሉን በፈጠረን አምላክ ስም በእነዚህ ተረጂ እናቶችና ህጻናት ስም በጣም አብዝተን እናመሰግናለን!!! ዋጋን ከሚከፍልከአምላክ ዘንድ በብዙ በረከት ተባረኩ!

* * * * * *

ልዩ ምሥጋና

የፈጠርከውን የማትረሳ ለአንተ ትርፍ ምህረትና የተትረፈረፈ በረከት እንጂ ትርፍ ሰው የሌለህ ሁሉም ያንተ ዋና የሆነ የሁሉ አምላክና የሁሉ አባት ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ: ዛሬም መላ ሲጠፋን ወዳንተ ጮህን ጊዜው ከፍቶ ባለበት እነዚህን ምስኪናን ሊራቡና መንገድ ሊወድቁ ነው ምን እናድርግ ስንል ፈጥነህ ሰማኸን በምንም ውስጥ መንገድ ያለህ ጌታ የሚታዘዙህን አነቃቅተህ ፈጣን ምላሽህን ስለሰጠኸን አምላክ እግዚአብሔር በእግርህ ሥር ተንበርክከን ፍፁም አክብሮታችን ምሥጋናችንን እናቀርባለ!!! እናምንሃለን ይህንክፉ ቀን ታሳልፈናለህ! ለነገም አንፈራም እንታመንሃለን!!!

*** *** ****

በፍቅር ለሕጻናት እና ስለእናቶች በጎ አድራጎት ምሥረታ እውን እዲሆን ገፍታችሁ ወደራዕዩ እንድንገባ ድፍረት ለሆናችሁን ላበረታታችሁን በገንዘብም በጉብኝትም ደግሞም ስለሥራችን ለሌሎች በመናገር ጉልህ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁት ወ/ሮ ዘነበች ተመስገን እና ባለቤታቸው አቶ አጥናፉ መንግሥቴን በፈጣሪ እና ፍቅርስም በጣም እናመሰግናለን:: ዘመናችሁ ይለምልም!

**** **** ****

ከምሥረታው አንስቶ ሥራውን ስንጀምር ደከመኝ ሳይል ድሆችን ከጎዳና ላይ ከመመልመል እስከ ቢሮ አደረጃጀት ድረስ ከጎናችን ያልተለየው ወንድማችን አቶ ገነነ ጣሰውን በፍቅር ስም በጣም እናመሰግናለን ብድራቱን አምላክ ይክፈለው!

**** **** ****

አምላክ ለፍቅር እስከዛሬ መቀጠል እንደምክንያት የተጠቀመበት ቅንነትና ትህትና የሞላው ሁሌም ዛሬም በመልካምነቱ ከጎናችን የማይለየው ወንድማችን አቶ ቆጠራ ዮሐንስን በህጸናቱና በእናቶች ስም እጅግ በጣም ልናመሰግነው እንወዳለን! አምላክ ዘመኑን ይባርክ::

**** **** ****

ስማችሁን ዘርዝረን ለማንጨርሰው ከቤተሰብ እስከ ወገኖቻችን በገንዘብ፣ በሙያ፣ በቁሳቁስ፣ በጉልበት የረዳችሁንና እየረዳችሁን ያላችሁ ወገኖቸ በቀና ልብ ካላችሁ ነገር ቀንሳችሁ ለወገኖቼ ይድረስ ብላችሁ ለለገሣችሁ በሙሉ ብድራታችሁን ከአምላክ አትጡት! በድሆች አምላክ ስም ከፍቅር በፍቅር መረቅናችሁ፣ ተባረኩልን፣ ክፉ አያግኛችሁ፣ የድሀሃን ባዶ ጎጆ ሞልታችሀኋልና ለዘላለም በረከት ቤታችሁ ይሙላ!!!

**** *** ****

ሁሌም ሆነ ዛሬም አብረውን በመሮጥ የደከሙ የተገኘውን ዕድል ሁሉ ለመልካም በመጠቀም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከማለዳ እስከማታ በመሥራት ከግዢ እስከ መመገብ ድረስ በሚገባ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ላሉት መልካምና ትጉዎቹ የአገልግሎቱ ባልደራባዎች፣ የራዕዩ ተካፋዮች ከበቡሽ አሰፋ፤ ስመኝ አስቻለው እና ሌሎች የፍቅር ሠራተኞች በሙሉ ፤ በፍቅር ስም በጣም አድርገን እናመሰግናችኋለን:: አምላክ ከበረከቱ ኑሮ ቤታችሁን፣ ህይወታችሁን የሙላ!!!

መሥራቾች ፀደቀ ጌታሁን እና ማርታ ወ/አረጋይ
*** *** ***

በመጨረሻም ብዙዎችን ለመታደግ የቆረጠው ደግና ታማኝ የሆነው በበጎ ሥራ ከእኔ ጋር ተጠምዶ ውስጤ ያለውን ሸክም የሚረዳኝና የሚረዳኝ፤ ከጉድለቱም እንኳ ቢሆን ሰጥቶ በማያቆም መቆረስና በሙሉ ልግስና፤ ገንዘቡን ጊዜውን እና እኔን ውድ ባለቤቱን ለዚህ በጎ ዓላማ በማካፈል የሚኖር የእግዚአብሔር ባርያ ውዱ ስጦታዬ ባለቤቴ ፀደቀ ጌታሁን (ወዳጅዬ) በጣም አመሰግናለሁ !!!በድሆች አምላክ ስም ተባረክልኝ ብድራትህ አይጥፋብህ!!!

የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ እና ባላደራ ማርታ ወ/አረጋይ


መልካምነት ዘር ነው በጊዜው ይበቅላል!!!
ፍቅር የተፍገመገሙትን ይደግፋል!!!
ፍቅር የወደቁትን ያነሳል!!!
እግዚአብሔር ፍቅር ነው!!!

ለተጨማሪ መረጃ

አዳዲስ ዘናዎችን አና ሁነቶችን ለማኘት ይመዝግቡ !

We don’t spam!