Skip to content
Home » እንኳን ደህና መጡ

እንኳን ደህና መጡ

በማንኛውም ምክንያት ወደዚህ ዌብ ሳይት ለመጎብኘት የመጣችሁ ክቡራንና ክቡራት ጎብኚዎቻችን አክብራችሁ የተወደደ ጊዜአችሁን ስለሰጣችሁን በፍቅር ለሕጻናትና ለእናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት ስም ከልብ እያመሰገንን እንኳን ደህና መጣችሁ እንላለን፡፡

የፍቅር ዓላማ

ድርጅቱ ለወገን የቆመና እንደ ሰው ለመኖር እድል ያጡትን በየቤቱ ጥጋትና በየመንገዱ ከእነልጆቻቸው ወድቀው የነበሩትን እናቶችና ሕፃናትን ከጎዳና እያነሳና ከልመና ጥገኝነት እያወጣ፤ ሕፃናቱን በሕፃናት መዋያ እያዋለ፣ እንዲሁም በልጆቻቸው ምክንያት ሥራ ከመሥራት ተገድበው አማራጭ ስለሌላቸው በተስፋ መቁረጥ በልመና ተሠማርተው የነበሩ እናቶችንም ድርጅቱ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ እራሳቸውን እንዲችሉና እንዲለወጡ እየተጋ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

ፍቅር ለሕጻናትና ለእናቶች ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የድርጅቱ መስራች በአዲስ አበባና አካባቢዋ ሕጻናት ልጆቻቸውን ታቅፈው ምጽዋት ሲለምኑ በሚመለከቷቸው እናቶች ልባቸው በመነካቱ እነዚህን ሕጻናትና እናቶች ማገዝ የሚችሉበትን መንገድ በማሰብ ያላቸውን ጥሪት ለዚሁ ተግባር በመመደብ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ዓላማቸውን በማስረዳትና የአጭርና ረጅም ግዜ እቅድ በመንደፍና በማስተባበር ባገኙት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በገርጂ አካባቢ በልመና ተግባር ላይ የተሰማሩ በርካታ እናቶችን በማነጋገር የባሰባቸውን በመምረጥ 10 ሕጻናትና እናቶችን በመርዳት አገልግሎቱን ጀምረዋል፡፡

ሂደት

ድርጅቱ ሕጻናቱን በመጠበቅ በመመገብና በመንከባከብ እናቶቻቸው ስራ እንዲጀምሩ የመስሪያ ገንዘብ፤ ስልጠናና መጠነኛ ተቀማጭ ገንዘብ በባንክ በማስቀመጥና በቁጠባ እንዲያሳድጉት በማድረግ፤ ለሌሎች እናቶች ስራ በመፍጠርና ተቀጠረው እንዲሰሩም ስራ በማፈላለግ ከልመና ተላቀው ራሳቸውን እንዲችሉ አድረጓል፡፡ ድርጅታችን ከቦሌ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 6፤ 7፤ 8፤9፤10፤ 13 እና 14 ጽ/ቤት እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በራሱ ሂደት አጣርቶ ትክክለኛ ችግረኞች መሆናቸውን በመለየት በአሁኑ ወቅት በጎ 40 ሕጻናትና35 እናቶችን በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡

ምስጋና

በዚህ ሁሉ የዚህን በጎ ሥራ ዓላማን በመደገፍ በገንዘብ፤ በዕውቀት፤ በጉልበት ድርጅታችንን በማስተዋወቅ የረዱንን ተቋማትና ግለሰቦችን ከፍቅር በፍቅር ስም ከከልብ እያመሰገንን አምላክ ብድራታችሁን በብዙ እንዲመልስ የዘወትር ፀሎታችን ነው!!

የተከበራችሁ የዚህ ዌብ ሳይት ጎብኚዎቻችን አክብራችሁ ስለጎበኛችሁን በድጋሚ እያመሰገንን የድርጅታችን ዓላማ በመገንዘብ በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ እህቶቻችንንና ልጆቻችንን በበለጠ መድረስ አንድንችል ወደፊትም ከጎናችን እንድትሆኑ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ባለንበት ቦታ ላይ መጥታችሁ በአካል እንድትጎበኙን እንጠየቃለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!!!
ፍቅር የወደቁትን ያነሳል!!!

Please Login to Comment.