መነሻ
ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችንና ህፃናትን አኗኗር ለማሻሻል አስተዋፅዖ ማድረግ ነው ፡፡ በልጆች አገልግሎት ላይ የተመጣጠነ ምግብ ፣ ጤና ፣ አልባሳት ፣ መሰረታዊ ትምህርት እና የተለያዩ የህፃናትን ክህሎት በእውቀት ማዳበር ነው፡፡ የሴቶች አገልግሎት ላይ ፣ የተለያዩ ዓይነት የሕይወት ክህሎት ሥልጠና በመስጠት ፣ የሥነ-ልቦና ድጋፍ ፣ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን እና የገንዘብ አቅርቦት በመስጠት ይደግፋል፡፡
አላማችንን ይደግፉ
አላማችን በችግር ምክንያት ተገፍተዉ በየጎዳናዉ ከነልጆቻቸዉ ወድቀዉ የነበሩትን እናቶችና ህፃናትን ከጎዳና አንስተን እንደ ማንኛዉም ሰዉ መሰረታዊ ፍላጎታቸዉ ተሟልቶላቸዉ እንዲኖር ማድረግ ነዉ፡፡
ፋንታዬ
ፋንታዬ እዘዘው ትባላለች: የመጣችው ከአማራ ክልል ሲሆን ቤተሰቦቿም ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የሚኖሩ ድሃ ገበሬዎች ናቸው ፡፡ ፋንታዬ በቀን ሰራተኛነት ወይም የቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምታገኘው ገቢ ህይወቷን ቀይራ ቤተሰቧን ለመርዳት ተስፋ በማድረግ አዲስ አበባ ገባች ፡፡ ከዚያ በመጀመሪያ የቀናት እና ያገኘችው የቤት ሠራተኝነቱ ነበር፡፡ የቤት ሰራተኛ ሆና መሥራት ጀመረች ፡፡
ስመኝ
ስመኝ በላይ ትባላለች፡- የመጣችው ከአማራ ክልል ሲሆን የተወለደችውም ከድሃ ቤተሰብ ነው ፡፡ ስመኝ ህይወቷን ቀይራ ቤተሰቧን ለመርዳት አስባ በጉልበት ሥራ ወይም በቤት ሰራተኛነት ሥራ ለመቀጠርና ገቢ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ አዲስ አበባ ገባች፡፡ ከዚያ መጀመሪያ የቤት ሰራተኛ ሆና መሥራት ጀመረች ፡፡ በዚያን ጊዜ ነበር ከበእምነት አባት ጋር ግንኙነት ጀመረች፡፡
ወርቄ
ተወልዳ ያደገችው እንጅባራ ወረዳ ገበሬ ማህበር ሲሆን የተወለደችውም ከድሃ ቤተሰብ ነው፡፡ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ህይወቷን ቀይራ ቤተሰቧን ለመርዳት አስባ በጉልበት ሥራ ወይም በቤት ሰራተኛነት ሥራ ለመቀጠርና ገቢ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ ከዚያ መጀመሪያ የቤት ሰራተኛ ሆና መሥራት ጀመረች ፡፡ ከዚ,ያም ባገኘችው የተሻለ ዕድል